የመንግስት አገልግሎት ዘርፍ ለውጥ ፍኖተ ካርታ የ10 ዓመት ዕቅድ ስልጠና

ለኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሰራተኞች የመንግስት አገልግሎት ዕሴት ግንባታና ስነ ምግባር ስልጠና በሰበታ ከተማ ተሰጠ፡፡ ስልጠናው በመንግስት አገልግሎት ዘርፍ የቀጣዮች 10 ዓመት የሚተገበር የለውጥ ፕሮግራሞች ላይ ግንዛቤ መፍጠር የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡ በተጨማሪም መንግስት የሚነድፋቸውን የልማት ዕቅዶች ማሳካት የሚችል የህዝብ አገልጋይነት መንፈስ የተላበሰ እና ነጻ፤ ገለልተኛና ብቃት ያለው የመንግስት አገልግሎት ሥርዓት መገንባት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡ የተሰጡንን ተግባርና ሃላፊነት ለመፈጸም የሰው ሀብት ልማት፤የአገልግሎት ማሻሻያ የሰው ብቃት አደረጃጀት መረጃን ማዘመን ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

በመጨረሻም ሰልጣኞች የሰው ሃብት ልማት ግንባታ ሃገራዊና ተቋማዊ ፋይዳውን በቡድን በመወያየት ሀሳባቸውን ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት