በስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ላይ በኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች እየተከናወነ ያለ ምርምር…!!!

የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በውሃ ዘርፍ አቅም ግንባታና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡ ኢንስቲትዩቱ በውስን የመንግስት ሀብት በየዓመቱ ለዘርፉ ውጤታማነት እየደገፋቸው ከሚገኙ ምርምሮች ባሻገር የራሱ ባለሙያዎችን አቅም በመጠቀም የተለያዩ ምርምሮች እየደገፈ ይገኛል፡፡

በኢንስቲትዩቱ በሚገኘው የስፔሻላይዝድ ላቦራቶሪ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት የተቋሙ ባለሙያዎች በስምጥ ሸለቆ ከሚገኙት ሀይቆች በላንጋኖ፤ ሻላ እና ዝዋይ ሐይቆች ላይ ያተኮረ ‘’Assessment of Water Quality by Using Physico-chemical and Microbiological Parameters. The Case of Central Rift Valley Lakes, Ethiopia’’ምርምር ለኢንስቲትዩቱ የስራ ሀላፊዎች፤ የማኔጅመንት አባላትና ባለሙያዎች አቅርበዋል፡፡

ከምርምር ፅሁፉ በኋላ የኢንስቲትዩቱ የስራ ሀላፊዎች ፤ የማኔጅመንት አባላትና ባለሙያዎች ሀሳብ አስተያየቶችና ጥያቄዎቻቸውን ለተመራማሪዎቹ አቅርበው ምላሾች የተሰጧቸው ሲሆን በቀጣይ ምርምሩ ተጠናቆ በሚቀርብበት ወቅት የተነሱ አንኳር ሀሳቦች ለምርምሩ መዳበር በግብአትነት እንደሚወሰዱ ተገልጿል፡፡

የምርምር ፅሁፉ በዋነኝነት በ3ቱ ሀይቆች ዙሪያ ከውሃ ጥራት ጋር ተያይዞ ባሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ምርምሩ ሀገራዊ ፋይዳ ያለውና ከሼልፍ በዘለለ ለሕብረተሰቡ ጠቀሜታ እንዲውል ተቋሙ ድጋፍ እንደሚያደርግ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ታመነ ሀይሉ በማጠቃለያ ሀሳባቸው ላይ ጠቅሰዋል፡፡

EWTI-PRCD-24-10-13 E.C