ኢንሰቲትዩቱ ሰልጣኞችን አስመረቀ፡፡

የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ “Well diagnosis and Rehabilitation” ፣ “Urban Sanitation” “Electromechanical” የተግባር ሥልጠና የሰጣቸውን ባለሙያዎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኘበት በዛሬው ዕለት አስመረቀ፡፡

ሰልጠኞቹ ኢንስቲትዩቱ ለሰጣቸው ዕድል አመስግነው በቆይታቸው ጠቃሚ ዕውቀት ማግኘታቸውን ተናግረዋል፤ ቢሰተካከሉ ያሉአቸውን ጉዳዮችም አክለዋል፡፡ የኢንተርኔት መቆራረጥ፣ የቴሌቪን አለመኖርና በአካባቢው ምግብ እንደ ልብ አለማግኘታቸው በሂደቱ ያጋጠሙአቸው ችግሮች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በምሥክር ወረቀት አሰጣጥ መርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬከተር አቶ ታምሩ ፈቃዱ በሰልጣኞቹ የተነሱ ጥያቄዎች የሚስተካከሉ መሀናቸውን ገልጸው ያለውን ሁኔታ አቸችለው ሥልጠናቸውን በማጠናቀቃቸው ሰልጣኞቹን አመስግነዋል፡፡

የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የኢንሰቲትዩቱ ዋና ዳይሬከተረ ዶክተር ታመነ ኃይሉ የኢንሰቲትዩቱ አሰልጣኞችና ሁሉም ሥልጠናው ላይ የተሳተፉ አካላት ለሥልጠናው መሰካት ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ በቀጣይም የተሻለ ሥልጠና ለመስጠት በሰልጣኞች የተነሱ ሀሳቦቸን እንደ ግብአት እንደሚጠቀም አክለው ገልጸዋል፡፡

(EWTI-PRCD- 28/05/2013 E.C)